ሐሸንገ ሐይቅ በትግራይ ብ/ክ/መ ከኮረም በ5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ተፈጥሯዊ መስህብ ሲሆን ማራኪ ከሚያደርጉት ሁኔታዎች መካከል አንዱ በከፍተኛ ቦታ ላይ በተራሮች መሃል ክብ ሠርቶ መገኘቱ ነው፡፡ በ2069 ሜትር ከፍታ ላይ አቅፈውት ያሉት እነዚህ ተራሮች ራሳቸው በትናንሽ የእርሻ ማሳዎች ተሸንሽነው ስለሚገኙ አይንን ይስባሉ፡፡ ከወደ ደቡብ ከሚያዋስነው ተራራ ጎን በደን በተሸፈነ ኮረብታ ላይ የማርያም ዓዲ ጎሎ ቤተ ክርስቲያን ትገኛለች፡፡ ይህም ሐይቁ ይበልጥ ተጨማሪ ውበት እንዲጎናፀፍ አስችሎታል፡፡ የሐይቁ ደቡባዊ ጠርዝ ላይ ምፍሳስ ባህሪ የሚባል ቦታ የ6ኛው ወይም በ7ኛው ክ/ዘመን ቤተ ክርስቲያን የያዘ የአርኪዮሎጂ ስፍራ ይገኛል፡፡ ሓሸንገና አካባቢው ኗሪና ስደተኛ ወፎችን በብዛት የሚያስተናግድ በመሆኑ የብዙ ተመራማሪዎችና ቱሪስቶችን ቀልብ ይስባል፡፡

ትግራይ ቱሪዝም መፅሔት